Feeds:
Posts
Comments

Archive for the ‘ዋልድባ ገዳም’ Category

ቀን 7 – 4 – 2006 ዓ.ም.

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን

በደላችንን በሞቱ፣ ሃጢያታችንን በቸርነቱ ያጠፋልን እስከ ሞት ድረስ የወደደን የአበው አምላክ እግዚአብሔር ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር የከበረ የተመሰገነ ይሁን አሜን።

መነኮሳይት እናቶች ከተገዛው አቡጀዲ ጋር ሆነው

መነኮሳይት እናቶች ከተገዛው አቡጀዲ ጋር ሆነው

 

ምንጊዜም ሠላምን ጠንነትን ለምንመኝላችሁ የቤተክርስቲያን እና የገዳማትእረዳት ለሆናችሁት የክርስቶስ ቤተሰቦች ለዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት ማኅበር በሙሉ ለተከበረው ውድ ጤንነታችሁ እንደምን ከርማችኃል እንደምን አላችሁልን እኛ ገዳማውያን መነኮሳይት ለጤናችን አምላከ አበው ይክበር ይመስገን ደህና ነን።

(more…)

Read Full Post »

የሰይጣን ውጊያው እንደቀጠለ ነው!
ዋልድባ
  • ·         ዘራቸውን እንደጣዖት የሚያመልኩ ካሕናት ተብዪውች ዋልድባን የመታደግ ጥረትን ለማደናቀፍ እየሞከሩ ነው
  • ·         በዋልድባ የቤተ ጣዕመ ክርስቶስ አባቶች ልማት አንቃወምም፥ ገዳሙንም አይነካም በማለት የአዞ እንባ እያነቡ ነው
  • ·         አፍቃሪ መንግሥት (ካድሬዎች) ዋልድባን ለመርዳት የሚደረገውን ጥረት ለመቃወም በየመንደሩ አሉባልታ እየነዙ ይገኛሉ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይም የኢትዮጵያ መንግሥት ታሪካዊውን እና ጥንታዊውን የዋልድባ ገዳም አፍርሶ የስኳር ፋብሪካ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት እንደገዳማዊ ገዳማውያን የሚባሉ፣ ነገር ግን ዘራቸውን እንደጣዖት የሚያመልኩ የበግ ለምድ ለብሰው በጠቦቶች መካከል የሚዘዋወሩ ተኩላዎች፥ ይህንን ታሪካዊ እና ጥንታዊ ገዳም ለመታደግ የሚንቀሳቀሰውን ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት (ዋልድባን እንታደግ) በመባል የሚታወቀውን ተቋም የተለያየ አሉባልታ በመንዛት ጥረቱን ለማደናቀፍ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ለመረዳት ችለናል።

ይህ ተቋም ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በተለያየ ጊዜ የዋልባ ገዳም አባቶች ላይ የመንግሥት ካድሬዎች የሚያደርሱባቸውን እንግልት፣ በደል፣ እና ስደት አቅም በፈቀደ ለመርዳት ይህ ተቋም ብዙ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል። ከነዚህም ጥረቶች መካከል ለመጥቀስ ያህል

፩ኛ/ ለአበረንታት መድኅኒዓለም ገዳም ለመርዳት $6000.00

፪ኛ/ ለዳልሻህ ኪዳነ ምሕረት ገዳም $3000.00

፫ኛ/ ለሰቋር ኪዳነ ምሕረት የእናቶች ገዳም መርጃ $2500.00

፬ኛ/ አባቶች እና እናቶች ወደጎንደር በተሰደዱ ጊዜ ለእህል ውሃ ማቅመሻ $500.00

፭ኛ/ እናቶች በአዲስ አበባ እርዳታ ለመጠየቅ በሄዱበት ወቅት ለእናቶች መርጃ የተላከ $800.00

፮ኛ/ ለዳልሻሕ ኪዳነ ምሕረት እናቶች ገዳም መርጃ የተላከ $4000.00

በጠቅላላ ለዋልድባ ገዳም የተላከው የገንዘብ መጠን እስከ ዛሬ ድረስ $16,800.00 መላኩን በመረጃዎች የተደገፈ ማስረጃዎች በእጃችን አሉ ነገር ግን እነዚህ ለመንግሥት እና ለቤተክርስቲያን ደብል ኤጀንት ሆነው እየሰሩ የሚገኙ ከሃይማኖታቸው ይበልጥ ለዘራቸው እና ለጎጣቸው አመዝነው በአብዛኛው ጊዜ ይህንን ጥረት ለመቃወም በተለያየ አውደ ምሕረት ላይ የሚናገሯቸው ነገሮች በእጅጉ የእነዚህን ዘረኞች ማንነት ልንመረመምር እና ልናውቃቸው እንደሚገባን ከወዲሁ ለመረዳት ችለናል። እነዚህ ሰዎች በየመንደሩ እየዞሩ፣ በየንሰሐ ልጆቻቸው ቤት በመሄድ እንዲሁም አጋጣሚውን ባገኙት ጊዜ ሁሉ ከሚናገሯቸው ንግግሮች መካከል ለአብነት ለመጥቀስ ያህል:

(more…)

Read Full Post »

የቆራሪት ከተማ

(አንድ አድርገን ታህሳስ 01 2006 ዓ.ም)፡- በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በዋልድባ ገዳም ላይ ለሚገነባው የስኳር ልማት ፕሮጀክት በመጀመሪያ ዙር 1800 አባወራዎች ከቦታቸው መነሳታቸው ታወቀ፡፡ ለተነሱ አርሶ አደሮቹ 127.5 ሚሊዮን ብር የካሳ ክፍያ ተሰጥቷል፡፡ ለእነዚህ ተነሺዎች ከወራት በፊት የገጠር ከተማ መልክ በመያዝ በተገነባችው የቆራሪት ከተማ ላይ የማስፈር ስራ ተከናውኗል ፡፡ ለዚች ከተማ ምስረታ ምክንያት ደግሞ በዋልድባ ገዳም ላይ የሚሰራው የስኳር ልማት ፕሮጀክት መሆኑ ታውቋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከቦታው የተነሱት 1800 ነዋሪዎች ከወልቃይት ወረዳ ፤ ከቃሌማ እና ፅምሪ ቀበሌ ይኖሩ የነበሩ አርሶ አደሮች ናቸው፡፡ መንግሥት እንደሚለው ለእነዚህ የልማት ተነሺዎች ለተነሱበት ቦታ በምትኩ የእርሻ ፤ የመኖሪያ  ቤት ፤ ሙሉ የቤት እና የሰብል ካሳ ክፍያ ፈጽሜያለሁ ብሏል፡፡ ለአርሶ አደሮቹ ነዋሪዎች መንግሥት 127.5 ሚሊየን ብር ካሳ መስጠቱ ታውቋል ፤ በሁለተኛ ዙር የሰፈራ ፕሮግራሙ ላይ 4ሺህ ሰዎች ከቦታው ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሰፈራው የሚቀጥል ሲሆን ለሚነሱት ከ13 ለማያንሱ አብያተ ክርስቲያናት ምትክ አዳዲስ ቤተክርስቲያን በቆራሪት ከተማ መሰራት መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

(more…)

Read Full Post »

ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከያዮች አንድነት (ዋልድባን እንታደግ) በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ በርድ ስታዲዮም በሚደረገው የሰሜን አሜሪካ የስፖርትና የባሕር ፌዴሬሽን 30ኛ ዓመት በዓል ላይ በመገኘት በዓሉ ላይ ለመገኘት ለሚመጡት ኢትዮጵያውያን ግንዛቤት በማስጨበጥ እና ተቋሙን ለማጠናከር የገቢ ማስገኛ ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛል። ይህ በዓል በኢትዮጵያውያን ዘመን አቆጣጠር ከሰኔ ፳፭ ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ ፳፱ ቀን ፳፻፭ ዓም (June 30 – July 6, 2013) የሚቀጥል ሲሆን በበዓሉም ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከመላው ዓለም የሚገኙበት ሲሆን ምዕመናን፣ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ልጆች፣ የቤተክርስቲያኒቷ ወዳጆች በርካታ እርዳታዎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል እያበረከቱም ነው ለዚህም አምላከ ቅዱሳን ዘወትር የማያልቅበትን በረከቱን ለምዕማናን እንዲያበዛልን እየተመኘን በሚቀጥሉት ሦስት ቀናትም ዝግጅቱ ስለሚቀጥል በዓለም ዙሪያ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በትብብራችሁ እንትበረቱ እና ቅድስት ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ከጥፋት፣ ገዳማት አድባራቱን ከምዝበራ፣ ንጹሐን መነኮሳትና መነኮሳይትን ከስደት፣ ዋልድባን ከመፈታት እንድንታደግ አደራ እንላለን።

በዚህ በዓል ላይ እጅግ በሚያኮራ እና በሚያስደስት ፍፁም የቤተክርስቲያን ቅንዓት ጫማዎችን በመጥረግ (ሊስትሮ)

 

DSC_2551 DSC_2566 DSC_2569 DSC_2571 DSC_2574 DSC_2577 DSC_2583

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

በማስጠረግ በርካታ ክርስቲያኖች ትብራቸውን እያደረጉ ነው በዚህም ቤተክርስያናቸውን ከጥፋት ለመታደግ፣ ዋልድባን እና የተለያዩ ገዳማትን ለመታደግ በሚደረገው እንቅስቃሴ ተባባሪነታቸው አሳይተዋል እና በመጨረሻው ዘመን አምላከ ቅዱሳን በክብር በሚገለጽበት ጊዜ “ኑ እናንተ የአባቴ ቡሩካን” ተብለው ከሚጠሩት ከቅዱሳን ወገን እንዲደምርልን ለአምላካችን ዘወትር በጸሎት እናመለክታለን።

 

 

 

በድንኳን 41 ፊትለፊት ይደረጋል ከ4:00 PM. ጀምሮ

በድንኳን 41 ፊትለፊት ይደረጋል
ከ4:00 PM. ጀምሮ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

በመጨረሻ በበዓሉ መጨረሻ ላይ ማለትም አርብ ሰኔ ፳፰ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. (July 5, 2013)  4:00 PM. ጀምሮ የግንዛቤ ማስጨበጫ ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ፈተናዎች እና የመንግሥት ተግዳሮት በሚል ርዕስ ዝግጅት ስለሚኖረን በድንኳን ቁጥር 41 ፊትለፊት በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል።

 

Let’s save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Read Full Post »

 

በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

  •      አንድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን የዋልድባ አባቶችን ለማነጋገር ወደ ወልድባ ከትላን በስቲያ ወደዚያው በማምራት ላይ ናቸው
  • ·        አቶ ሸዊት የማይጸብሪ የፖለቲካ መምሪያ ሃላፊ ለአባ ገብረሕይወት መስፍን ቀጭን ትዕዛዝ ሰጥተዋል
  • ·        ነገ የሚገባው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ግሩፕ የሚያነጋግረው እነ አቶ ሸዊት እና አባ ገብረሕይወት ያዘጋጇቸውን የሐሰት መነኮስት ቡድን ነው
  • ·        እስከ አሁን ድረስ ከስድሳ በላይ መነኮሳት ከዋልድባ ገዳም በግፍ ተግዘው በተለያዩ የኢትዮጵያ ገዳማት ተሰደው ይገኛሉ
  • ·        እነ አባ ገብረሕይወት ሶስት የጎጠኛው ቡድኖችን ለሰብዓዊ መብት ተሟጋች ግሩፑ መልስ እንዲሰጡ አዘጋጅተው እየጠበቁ ነው

(more…)

Read Full Post »

 

“በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁበፊቱ ተጠንቀቁ፥ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት። አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ፥ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፥ ጠላቶችህን እጣላቸዋለሁ፥ የሚያስጨንቁህንም አስጨንቃቸዋለሁ።” ዘጸዓት ፳፫ ፥ ፳፩-፳፪

  • በዋልድባ የሰራተኞች መኖሪያ የቅዱስ ሚካኤል እለት ንፋስ በቀላቀለ ንፋስ ተጠራርጎ ጠፍቷል
  • የዋልድባ መነኮሳት ማኅበረ ቤተ-ሚናስ ተወካዮች ቅዱስ ፓትርያሪኩን አነጋገሩ
  • “እኔ ጉዳዩን አላውቀውም፣ ከሌሎች አባቶች ተወይቼ መልስ እንሰጣችኋለን” ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ
  • በአፋር እና ትግራይ ክልል አካባቢ የሚገኘው ታሪካዊ እና እድሜ ጠገብ የመዝባ ገዳም ሆን ተብሎ እሳት ተለኮሰበት፣ አንድ ቤተመቅደስ ተቃጥሏል ሌሎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል መነኮሳቱም ወደ ትግራይ ክልል መሪዎች አቤት ብለዋል

ዘገባውን በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ 

 ኢሮብ-ትግራይ
ኢሮብ ትግራይ

(more…)

Read Full Post »

ገዳመ ዋልድባ ላለፉት 1600 ዓመታት ተከብሮ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ እኛ ላይ ደርሶ ነበር። በአሁን ሰዓት መንግሥት በልማት ሰበብ ሸንኮራ አለማለሁ፣ እምነበረድ ፋብሪካ አቋቁማለሁ፣ የወርቅ ማዕድን ማውጫ እሰራለሁ፣ ወዘተ በማለት ልማት እያለ ታላቁን፣ ታሪካዊውን የኢትዮጵያ ሃብት ለማጥፋት ብሎም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካሕናት፣ ዲያቆናት፣ መነኮሳት፣ ቆሞሳት እና ጳጳሳት ምንጭ የሆነውን ገዳም ለማድረቅ እና ለማጥፋት ወገቡን ታጥቆ ከተነሳ ሰንበት ብሏል። ኢትዮጵያውያንም ለሃይማኖት የማይቆረቆር ግዴለሽ ትውልድ ሆኗል እና ዛሬ የመፍረስ እና የመበተን ፍርድ የተፈረደበት ገዳም ገዳማውያን ያለጥፋታቸው እየታሰሩ፣ እየተደበደቡ፣ እንደወንጀለኛ ያለፍርድ በየእስር ቤቱ እየታጎሩ ይገኛሉ፣ ታዲያ ማነው ለምን ብሎ ሊጠይቅ የሚገባው እኛ አይደለንም እንዴ አንዱ በሬዲዮ “ገዳሙን አንነካም ብለዋል” ይለናል እነሱማ ሁሉንም ይላሉ አረማውያን ጸሐፍት ፈሪሳውያን ጌታን ሲሰቅሉት እኮ ምክንያት አበጅተው ነው ሕይወት የሚሆናቸውን ሰቀሉት ዛሬም የኛ ሰው ለመጪው ትውልድ ታሪክ ማጣቀሻ የሚሆነውን ብርቅ እና ድንቅ ገዳም ለማፍረስ ደፋ ቀና ይላሉ እውን እነዚህ ለኢትዮጵያ አሳቢዎች ናቸው?? ትልቅ ጥያቄ ነው ዛሬ ታሪኮቻችንን ቅርሶቻችንን እና ብርቅና ድንቅ የሃገራችንን ሃብቶች ቀስ በቀስ እያጣናቸው ነው ማን ይጠይቅ?
ትላንት የአቡነ ጴጥሮስን ሃውልት አፈረሱ እውን እቦታው ይመለስ ይሆን? ሁላችንም የምንመለከው እውነታ ነው
የሉሲ ቅሪት በጉብኝት ሰበብ በብዙ ሚሊዮን ብሮች ወጥታለች ትመለስ ይሆን?
እድሜ ጠገብ የሆኑት የብራና መጻሕፍት የወርቅና የብር መስቀሎች ከየገዳማቱ እየተዘረፉ ለገባያ ውለዋል ማን ይጠይቅ
ልብ ያለው ልብ ይበል

Let’s save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!

Read Full Post »

አቶ አባይ ጸሀይ በአባ ወልደ ማርያም አማካኝነት ከዋልድባ መነኮሳት ጋር ተነጋገሩ

  • መናኝ ኃይለመለኮት ከእስር ተፈቱ፥ ነገር ግን በአስቸኳይ ገዳሙን ለቀው እንዲወጡ ተነገራቸው
  • ከትንሳኤ በኃላ ከገዳሙ የሚባረሩ እንደሚኖሩም ተጠቁሟል
  • ማቄን ጨርቄን ሳትሉ ቦታውን ጥላችሁ ውጡልን

 በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ 

ባለፈው አርብ እለት ማታ በተከሰተው በታጣቂዎች በማይለበጣ እናበዳንዶሮቃ ዘረፋ ከተፈጸመ በኃላ በቀጣዩ እለት ማለትም ቅዳሜ መናኝ ኃይለመለኮት የተባሉትን አባት ያለ ጥፋታቸው ወደ ማይጸብሪ በመውሰድ በእስር ላይ እንደነበሩ ይታወሳል። በእለቱ አሉ ተብለው ለእስር የዳረጋቸውም “ታጣቂዎች ይዘርፉናል፥ ታጣቂዎች የዳኙናል” በሚል ሰበብ እንደነበረ ዘግበን እንደነበረ ይታወሳል። በዚሁ እለትም በታጣቂዎች ተደብድበው የሕክምና እድል እንኳን ማግኘት ያልቻሉትንም አባ ፍቅረማርያምን እስከ አሁን ድረስ ደማቸውን ከሚጠራርጉላቸው ወንድሞቻቸው በቀር የረባ ሕክምና ወደ ማይጋባ ወስደን እናሳክም ብለው የጠየቁትን “አይመለከታችሁም አርፋችሁ ተቀመጡ” በማለት ማስፈራራት ደርሶባቸዋል፥ እኝህ አባትም እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ምንም አይነት ህክምና ሳያገኙ መቆየታቸውን ስጋታቸው አባቶች ገለጸውልናል፥ ነገር ግን ከሰዎቹ ፈቃድ ውጪ ምንም ለማድረግ አለመቻላቸውም በእጅጉ አሳዝኗቸዋል።

 

ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ቅዳሜ የታሰሩት መናኝ ኃይለመለኮት ከታሰሩበት እስር ቤት ቀጭን ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ወጥተዋል። በትዕዛዙ መሰረትም መናኝ ኃይለመለኮት ወደ ገዳሙ የመግባት ፈቃድ እንደሌላቸው እና በቀጥታ ወደሚሄዱበት እንዲሄዱ አሳሪዎቻቸው አስፈራርተው ነግረዋቸዋል። ከጥቂት ወራት በፊት ወደ አርባ የሚጠጉ አባቶች እና እናቶች የሚደርስባቸውን በደል በባሕርዳር ለአማራ ክልል ፕሬዘዳንት ቢሮ፣ ለክልሉ የጸጥታ ክፍል፣ ለክልሉ የፓሊስ ኮሚሽነር ቢሮ፣ በጎንደር ከተማ ለሚገኙት ለሰሜን ጎንደር ሃገረ ስብከት ጽ/ቤት፣ ለሰሜን ጎንደር የጸጥታ ቢሮ አቤቱታቸውን እንዳሰሙ ይታወሳል፥ በመጨረሻም የሰሜን ጎንደር ሃገረ ስብከት ጸሐፊ፣ የሰሜን ጎንደር የጸጥታ ክፍል ሃላፊዎች ከማይጸብሪ አስተዳዳሪ ጋር በመነጋገር ችግራችሁን እዛው ሄደን ተነጋግረን እንፈታዋለን ተብለው ሳይፈልጉ በግድ ከጎንደር ተግዘው (ተገደው) ማይጸብሪ ተወስደው የስድብ እና ማንጓጠጥ መዓት ወርዶባቸው ወደ ገዳማቸው እንደገቡ ይታወሳል። ከገቡም በኃላ በየእለቱ ተደጋጋሚ ማስፈራሪያ ደርሶባቸው የበረቱት በውድቅት ሌሊት ሕይወታቸውን ለማቆየት ከገዳሙ ተሰደው በተለያዩ የክልሉ ገዳማት ገብተው እንዳሉ ለመረዳት ችለናል። ቅዳሜ እለት ለእስር የተዳረጉት መናይ ኃይለመለኮትም በወቅቱ ማስፈራራት ከደረሳቸው አባቶች መካከል አንደኛው ሲሆኑ፣ የሚመጣውን እንደጌታዬ እየሱስ ክርስቶስ በጸጋ እቀበለዋለሁ ብለው በገዳሙ ቆይተው እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በዚህም ምክንያት ሳይሆን እንደማይቀር አንዳንድ አባቶች ይገምታሉ መናኝ ኃይለመለኮትን ለእስር ያበቃቸው እንጂ ከሳሾቻቸው (ታጣቂዎቹ) እንደሚሉት “ታጣቂዎች ዘረፉን፥ ታጣቂዎች ይዳኙናል” የሚለውን ቃል እሳቸው እንዳልተናገሩ ለመረዳት ችለናል።

(more…)

Read Full Post »

  • ማይለበጣ ቤተ-እግዚአብሔር በታጣቂዎች ተዘረፈ
  • ·         ዶንዶሮቃ ላይ የሚገኘው የዋልድባ ገዳም ወፍጮ ቤትም በተመሳሳይ ታጣቂዎች ተዘርፏል
  • አባ ፍቅረማርያም የተባሉ አባት በደረሰባቸው ከባድ ድብደባ በህክምና ላይ ናቸው
  • መናኝ ገብረመድኅን የተባሉ ስመ እግዚአብሔር ጠርተው ለምነው ከድብደባ ድነዋል
  • መናኝ ኅይለመለኮት የተባሉ አባት “ታጣቂዎች ዘረፉን፣ ደበደቡን፥ ታጣቂዎችም ሊዳኙን መጡ” ብለዋል በሚል ወደ እስር ቤት ተጥለዋል

 

እለቱ አርብ ሚያዚያ ፲፩ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. ማታ ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ሲሆን ጭልም ድቅድቅ በሆነበት ሰዓት ላይ ማይለበጣ በሚገኘው ቤተ እግዚአብሔር ላይ በከባድ የሚሊተሪ ልብስ እና ትጥቅ የታጠቁ በግምት ስድስት የሚሆኑ ታጣቂዎች በውጪ በረንዳ ላይ ተኝተው የነበሩትን መነኮሳት እና መናንያን ደብድበው እና ብዙ እንግልት አድርሰውባቸው ገንዘብ ያለው የት ነው ተናገሩ በሚል ብዙ እንግልት እና ድብደባ እንዳደረሱባቸው ከቦታው በደረሰን መረጃ መመልከት ችለናል። በመጨረሻም ታጣቂዎቹ ከመሄዳቸው በፊት ጽ/ቤቱን በሰደፍ ሰብረው ሲያበቁ በጽ/ቤት ውስጥ ያለውን ንብረት በመወርወር ሲያምሱ ቆይተው ምንም ባለማግኘታቸው ተበሳጭተው መነኮሳቱን ደብደበው እና አንገላተው ጥለው ወጥተው ለመሄድ ችለዋል።

(more…)

Read Full Post »

  • የአዲርቃይ ፍርድ ቤት ገዳማችን አይታረስም በማለታቸው ወጣቶችን በአሸባሪነት ከሰሰ
  • በዛሬማ የሚገኙ ነዋሪዎች በወጣቶቹ ላይ ምስክርነት አንሰጥም በማለታቸው እንግልት እየደረሰባቸው ነው
  • የሰሜን ጎንደር ጸጥታ ክፍል ክሱ በአሸባሪነት መሆን አለበት በማለት ትዕዛዝ አስተላልፏል
  • የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከገዳሙ በረከት ለመቀበል የመጡት ማስፈራሪያ እና ፍተሻ (strip search) ተደረገባቸው
  • የጣሊያኑ ኮንስትራክሽን ሌላ አማራጮችን እንፈልግ ብሏል
  • የወልቃይት ነዋሪም እርሻውን እንዲቀጥል እስከሚመጣው ዓመት ምንም ነገር እንደማይኖር እየተነገረው ነው

ሙሉውን በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ 

ethiopian-sugar-corporation-projects-map

የዛሬ ዓመት አካባቢ ይሆናል የዛሬማ ወጣቶች ከመንግሥት ጋር ገዳማችን አይታረስም፣ የአባቶቻችንን ድንበር አናስነካም በማለት ከመንግሥት ታጣቂዎች ጋር ግብግብ የተፈጠረው፥ በወቅቱ የክልሉ ባለሥልጣናት በቦታው ተገኝተው ከዛሬማ ነዋሪዎች ጋር ስብሰባ አድርገው የዛሬማን ነዋሪ ውሳኔ እንዲሰጥ እያስፈራሩ ባሉበት ወቅት ነበር ጥቂት ወጣቶች የአባቶቻችንን ድንበር አናስነካም፣ ገዳማችንንም ፈቅደን አናሳርስም በማለታቸው ጥቂቶቹን በወቅቱ ወደ እስር ቤት ሲከቷቸው የተቀሩት አምልጠው ጫካ ገብተው ገዳማችንን ማንም ሊነካውም፣ ሊደፍረው፣ ሊረግጠውም አይገባም በማለት ጥሪያቸውን ሲያቀርቡ ቆይተዋል የአካባቢውንም ገበሬ ማኅበራት፣ የሃገር ሽማግሌዎችን በማነጋገር እንዴት ዓይናችን እያየ ገዳማችንን የማንም አማቄላውያን (አረማውያን) መፈንጫ ይሆናል፣ ይሄ ቦታ እኮ የቅዱሳን ማረፊያ፣ የግዑሳን መጠጊያ ለእኛ ለተዳደፍነው እረፍት፣ በረከት፣ ቅድስና ለማግኘት የምንሄድበት እንጂ እንዴት እነዜህ አረማውያን ዛሬ እንደፈለጉት ያደርጉታል በማለት ተቃውሟቸውን በከተማው አስተዳደር ጽ/ቤት ከሃገረ ስብከቱ ሃላፊዎች ቢያቀርቡም የተወሰኑ የመንግሥት ሃላፊዎች በሃገር ሽማግሌዎች ምከሯቸው እና ወደ ቤታቸው እና ቤተሰባቸው ይመለሱ በማለት አግባብተው ወደ ሃገራቸው እና ቤተሰባቸው ከተቀላቀሉ የሦስት ወይም ሁለት ወር አይበልጣቸውም ነበር።

 

የኢትዮጵያ መንግሥት ሊያስገነባቸው ያሰባቸው የስኳር ፋብሪካዎች

ወጣቶቹም ወደ ሃገራቸው እና ወደ ቤተሰቦቻቸው እንደተመለሱ ብዙም ሳይቆይ የአዲርቃይ ከተማ አቃቤ ሕግ ቢሮ ደብዳቤ ከሰሜን ጎንደር የጸጥታው ቢሮ ይደርሰዋል በደብዳቤውም ላይ “ከዚህ በፊት ታስረስው እና በምሕረት የተመለሱት ወጣቶች በሙሉ በአሸባሪነት፣ በመንግሥት ላይ በመነሳት፣ እና ከግንቦት 7 ታጣቂዎች ጋር በመተባበር” በአስቸኳይ እንዲከሰሱ እና የፍርዱንም ሄደት እንደሚከታተሉት ጠቅሰው ደብዳቤ ይጽፋሉ። ደብዳቤ የደረሳቸው የአቃቢ ሕጉ ቤሮ ሰራተኞች ወደ ዛሬማ በመሄደ ከከተማው የመንግሥት ተወካዮች እና የጸጥታው ሃላፊዎች ጋር መመካከር ይጀምራሉ፥ የዛሬማ ከተማ መስተዳደር እና የጸጥታው ሃላፊዎች እንዴት ብለን ነው በአሸባሪነት የምንከሳቸው? በምን መረጃ ነው ብለው ሲጠይቁ ሰዎችን አስመስክሩባቸው በማለት የአቃቢ ሕጉ ሰራተኞች ቢጠይቁም ጥቂት የአካባቢው ነዋሪዎች ተጠርተው የምስክርነት ቃላቸውን እነሱ በሚፈልጉት መልኩ ከመሰከቱ ወሮታውን መንግሥት እንደሚሰጣቸው ቢያብሏቸውም “እኛ በልጆቻችን ላይ የሃሰት ምስክር ልንሆን አንችልም፣ የምናውቀው ነገር ቢኖር ገዳማችንን አትንኩ ማለታቸውን ነው በማለት እንቢታቸውን ገልጸዋል” የአካባቢው ነዋሪዎችም እንሰዛሬ ድረስ ሰዎችን እንዲህ እየደረጉ ነው ለካ በሃሰት እየከሰሱ ያሉት እነኝህ ወጣቶች ያደረጉት ነገር ቢኖር ገዳማችን አትንኩ ከማለት በስተቀር እንኳን አሸባሪ ሊሆኑ ጭራሽ እንዴት እንዲህ ዓይነት ክስ ሊመሰርትባቸው ይችላል በማለት ቅሬታቸውን ደጋግመው በማሰማት የአካባቢው የጸጥታ ቢሮ እና የአዲርቃይ የአቃቢ ሕግ ሰራተኞች ተመካክረው ወጣቶቹን በአሸባሪነት ቀርቶ በሌላ ክስ ሊመሰርቱባቸው ተስማምተው ነበር ጉዳዩ

(more…)

Read Full Post »

Older Posts »