ገዳመ ዋልድባ ላለፉት 1600 ዓመታት ተከብሮ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ እኛ ላይ ደርሶ ነበር። በአሁን ሰዓት መንግሥት በልማት ሰበብ ሸንኮራ አለማለሁ፣ እምነበረድ ፋብሪካ አቋቁማለሁ፣ የወርቅ ማዕድን ማውጫ እሰራለሁ፣ ወዘተ በማለት ልማት እያለ ታላቁን፣ ታሪካዊውን የኢትዮጵያ ሃብት ለማጥፋት ብሎም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካሕናት፣ ዲያቆናት፣ መነኮሳት፣ ቆሞሳት እና ጳጳሳት ምንጭ የሆነውን ገዳም ለማድረቅ እና ለማጥፋት ወገቡን ታጥቆ ከተነሳ ሰንበት ብሏል። ኢትዮጵያውያንም ለሃይማኖት የማይቆረቆር ግዴለሽ ትውልድ ሆኗል እና ዛሬ የመፍረስ እና የመበተን ፍርድ የተፈረደበት ገዳም ገዳማውያን ያለጥፋታቸው እየታሰሩ፣ እየተደበደቡ፣ እንደወንጀለኛ ያለፍርድ በየእስር ቤቱ እየታጎሩ ይገኛሉ፣ ታዲያ ማነው ለምን ብሎ ሊጠይቅ የሚገባው እኛ አይደለንም እንዴ አንዱ በሬዲዮ “ገዳሙን አንነካም ብለዋል” ይለናል እነሱማ ሁሉንም ይላሉ አረማውያን ጸሐፍት ፈሪሳውያን ጌታን ሲሰቅሉት እኮ ምክንያት አበጅተው ነው ሕይወት የሚሆናቸውን ሰቀሉት ዛሬም የኛ ሰው ለመጪው ትውልድ ታሪክ ማጣቀሻ የሚሆነውን ብርቅ እና ድንቅ ገዳም ለማፍረስ ደፋ ቀና ይላሉ እውን እነዚህ ለኢትዮጵያ አሳቢዎች ናቸው?? ትልቅ ጥያቄ ነው ዛሬ ታሪኮቻችንን ቅርሶቻችንን እና ብርቅና ድንቅ የሃገራችንን ሃብቶች ቀስ በቀስ እያጣናቸው ነው ማን ይጠይቅ?
ትላንት የአቡነ ጴጥሮስን ሃውልት አፈረሱ እውን እቦታው ይመለስ ይሆን? ሁላችንም የምንመለከው እውነታ ነው
የሉሲ ቅሪት በጉብኝት ሰበብ በብዙ ሚሊዮን ብሮች ወጥታለች ትመለስ ይሆን?
እድሜ ጠገብ የሆኑት የብራና መጻሕፍት የወርቅና የብር መስቀሎች ከየገዳማቱ እየተዘረፉ ለገባያ ውለዋል ማን ይጠይቅ
ልብ ያለው ልብ ይበል
Let’s save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!
Leave a comment