የዋልድባ ጉዳይ “ሳይቃጠል በቅጠል”
የዋልድባ ገዳም ፈተና ክፍል ፬ እና የመጨረሻው ክፍል
የዋልድባ ገዳም ፈተና ክፍል ፫
የዋልድባ ገዳም ፈተና ክፍል ፪
የዋልድባ ገዳም ፈተና ክፍል ፩
የዋልድባ ገዳም አመሠራረትና ታሪክ፣ ዋልድባ ገዳም በዛሬማ፣ በማይዘሁል፣ በእስያ፣ እና በተከዜ ወንዞች የተከበበ ታሪካዊ ገዳም
ነው፣ ገዳሙም ከተመሠረት ከ1600 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን በአሁን ሰዓት በውስጡ ከ3000 በላይ መናኒያን ሲኖሩ
(ስውራኑን መናኒያን ሳይቆጠር) የሚሩበት ገዳም ነው በገዳሙ ውስጥ ስቋር፣ አበረንታት፣ አባ ነፃ፣ ደሻል፣ ቤተ ሚናስ፣ የሚባሉ
ገዳማት ያሉበት ቦታ ነው። በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ መንግሥት የስኳር ፋብሪካ እንዲሁም ፖርክ ይዞታ እንገነባለን በማለት በዚህ
በቅዱስ ቦታ ላይ በግምት ወደ 50,000 ሰዎችን ለማስፈር በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፣ እንደ መንግሥት ገለጻም በሚቀጥሉት 5
ዓመታት ውስጥ ግንባታው ከተጠናቀቀ ዋልድባ የሚባለው ቅዱሱ እና ከገዳማት ሁሉ ታሪካዊውና ቅዱሱ ገዳም ለመጨረሻ ግዜ ሕልውናው
በከባድ ጥያቄ ላይ ይወድቃል።
መንግሥታችንን የምንጠይቀው በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ያልታረሱ እና ያልለሙ ድንግል መሬቶች እያሉ
ወንዞቹም የሰውን ሃገር የሚያጠጡት እንደነ ዋቢሸበሌ አባይ እንዲሁም ተከዜ እያሉ ለምን ወደ ዋልባ ገዳም ድረስ በመምጣት ይህንን
እኩይ ሥራ ለመሥራት ተገደዳችሁ? የሳዑዲ ገንዘብ ወይስ እግዚአብሔርን መዳፈር? መልሱን ለመንግሥታችን እንተወውና. .
.
እያንዳንዱ ሀገር ወዳድ፣ የቅርስ እና የትውፊት ተቆርቋሪ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ኦርቶዶክስ እስላም ክርስቲያን በሙሉ የቅርስ
ተቆርቋሪ የሆናችሁ በሙሉ ለዚህ ሀገረዊ ጥሪ በያላችሁበት ሀገራዊ ምላሻችሁን እንደምትሰጡ እናምናለን።
እግዚአብሔር አምላክ
ኢትዮጵያን ይጠብቃት አሜን
Leave a comment