Feeds:
Posts
Comments

Archive for July, 2012

  • READ THIS ARTICLE IN PDF.
  • ከአብረንታንትእናማይለበጣሁለትመነኰሳትወደማይፀብሪተወስደዋልበዶንዶሮቃ50 በላይየመነኰሳትእናመነኰሳዪያትቤት በፖሊስተፈትሿል
  • ከፖሊሶቹ አንዲቱ ከጾታዋ የተነሣ ወደ ዋልድባ ለመግባት የማይፈቀድላት ሴት ናት
  • የአብረንታንቱአባገብረሥላሴዋለልኝእንደታሰሩናቸው
  • 49 ያላነሱየቤተሚናስመነኰሳትበፖሊስይፈለጋሉ
  • ‹‹እናንትምታታሞችለጠቅላይሚኒስትሩመታመምተጠያቂዎችናችሁ›› /የማይፀብሪፖሊሶች/
(ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ23/2004 ዓ.ም፤ ጁላይ30/ 2012)ምሽቱንወደገዳሙበገቡትዐሥርያህልየማይፀብሪፖሊሶችና ታጣቂዎች የተወሰዱትሁለትመነኰሳትአባወልደጊዮርጊስከዋልድባአብረንታንትመድኃኔዓለም፣አባገብረማርያምጎንዴከማይለበጣ (የማኅበረ መነኰሳቱ ሰፊውየአትክልትቦታ) ናቸው፡፡ሁለቱአበውመነኰሳትበፖሊሶቹተይዘውከመወሰዳቸውአስቀድሞበኣቶቻቸውበፖሊሶቹፍተሻእንደተካሄደበትተገልጧል፡፡ ከፖሊሶቹ አንዲቱ ከጾታዋ የተነሣ ወደ ዋልድባ ለመግባት የማይፈቀድላት ሴት መኾኗ የወረዳው አስተዳደር ለገዳሙ ትውፊታዊ ሥርዐትና ክብር መጠበቅ ያለውን የወረደ ግንዛቤ የሚያሳይ ነው፡፡
Advertisements

Read Full Post »

በሰሜኑ የሃገረችን ክፍል በሚገኘው በታላቁ የዋልድባ ጉዳይ ላይ በርካታ የሆኑ ኢ-ሰብዓዊ የሆኑ ድርጊቶች በገዳሙ እና በገዳማውያኑ ላይ ሲደርስ ቆይቷል እንደቀጠለም ነው። እግዚአብሔር በእርግጥ በዚህ ታሪካዊና ቅዱስ ገዳም ላይ ፊቱን እንደማያዞር እምነታችን ቢሆንም ነገር ግን በገዳማውያኑ ላይ የሚደርስባቸው እንግልት በተፋጠነ ሁኔታ መቀጠሉ የችግሩን ግዝፈት ያሳየናል። ዛሬ ዛሬ ጭራሽ ሰውም በዜናው በመሰላቸት ይመስላል ዝምታው ቀጥሏል። እነዚህ ገዳማውያን ለሃገር ለወገን ለመሪዎች እንዲሁም በአጠቃላይ ለዓለም ሰላም በፀለዩ፣ እህል ስፈሩልን፣ ገንዘብ ቁጠሩልን ሳይሉ ከፈጣሪ ጋር ዕለት ተዕለት በጸሎት እና በስግደት በተገናኙ ምን በደል ኖሮባቸው ይሆን ይህ ሁሉ በደል፤ እንጀታቸው በቋርፍ ተጣብቆ የሚኖሩ አባቶቻችን ዛሬ ጀርባቸው በግርፋት፣ እጅና እግራቸው ለእግረ ሙቅ ለምን እንደተዳረጉ እንቆቅልሽ ሆኖብን ነው።

ዛሬ ለምን ይህን አላችሁ እንደምትሉን እርግጠኞች ነን፥ በትላንትናው ዕለት በዚሁ በታላቁ ገዳም አበረንታት ገዳም አካባቢ የመንግሥት ታጣቂዎች በመግባት መነኩሳቱን ለእስር እና ለግርፋት መዳረጋቸውን ከአካባቢው ባሉን ምንጮች ደርሶናል በዚህ በትላንቱ የመንግሥት ታጣቂዎች በርካቶች ሲታሰሩ ይልቁንም የእቃ ቤቱ ሃላፊ አባ ገብረ ማርያም እና ሌሎች መነኩሳት ታስረስ ወደ ማይ ጸብሪ ወረዳ ለእስር ተወሥደዋል፤ በዚህም የተነሳ ይመስላል ወደ 49 የሚደርሱ መነኩሳት ሱባኤ አቋርጨው ወደ ማይ ጸብሪ ወረዳ አቤቱታቸውን ለማቅረብ ሄደዋል። ልክ ከዚህ በፊቱ እንደሆነው እነኝህ ታጣቂዎች መነኩሳቱን ለእስር ሲወስዷቸው በድብደባ እና በማንገላታት ነው ይህንን ለተመለከተ ህግ እና ፍትህ በሃገራችን ላይ እንደጠፋ ለማንም ግልጽ ነው። ገዳማውያኑ የአንድ ዜጋ መብት እንኳን መብት ሳይጠበቅላቸው እንደ ወንጀለኛ እየተገረፉ እና የተሰደቡ መወሰዳቸው የማንንም ንጹህ ህሊና ያለውን ሰው አእምሮ እንደሚያሳምም ግልጽ ነው።

(more…)

Read Full Post »

  • አንድ የዋልድባ አብረንታንት ገዳም መነኰስ ወደ ማይ ፀብሪ ተወስደዋል።
  • የገዳሙ መነኰሳት የግዴታ መታወቂያ እንዲወስዱ ተደርገዋል።
  • ፓትርያርኩ ዕግድ የጣሉበት የጀርመን የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሒዷል።

(ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 14/2004 ዓ.ም፤ ጁላይ 21/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት በዋልድባ ገዳም ህልውናና ክብር ላይ በሚያደርሰው ተጨባጭ አደጋና ታሳቢ ስጋቶች የተነሣ የፕሮጀክቱን አተገባበር በሚቃወሙ የዋልድባ ማኅበረ መነኰሳት ላይ የሚደርሰው እስር፣ እንግልትና ድብደባ ተባብሶ መቀጠሉን የሥፍራው ምንጮቸ ለደጀ ሰላም ገልጸዋል፡፡ በተለይም የፀለምት – ማይ ፀብሪ ወረዳ አስተዳደር በየጊዜው በመነኰሳቱ ላይ በሚወስደው የግፍ ርምጃ በሠቆቃ ውስጥ የሚገኙት ማኅበረ መነኰሳቱ ከሰኔ 21 – ኅዳር 8 ቀን የሚዘልቀው የገዳሙ የሱባኤ ወቅት እንደታወከ ተዘግቧል፡፡
(more…)

Read Full Post »

ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በዋሽንግተን ዲሲ

በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ለምትኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኞች በሙሉ፥ እንደሚታወቀው ቅድስት ቤተክርስቲያን በበርካታ ዘመን ወለድ ችግሮች፣ በአስተዳር፣ እና በተለያዩ ተጽዕኖዎች ውስጥ እንዳለች ይታወቃል፥ ሆኖም ችግሮቿን በግልጽ ተነጋግሮ ለችግሮቹም የመፍትሄ ሃሳብ ማምጣትም፣ መፍትሄም መሆን የሚችለው ደግሞ አማኙ እንደሆነ እሙን  በመሆኑ ፤ ዋልድባን ለመታደግ የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ ኮሚቴ የዋሽንግተን ዲሲ ንዑስ ክፍል በመጪው 
ነሐሴ ፮ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. (August 12, 2012) በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው 
Saint George Ball Room and Conference room
4335 16th Street, NW.
Washington, DC 20011 ታላቅ መንፈሳዊ ዝግጅት አዘጋጅቷል፥ በዝግጅቱም ላይ በርካታ የቤተክርስቲያኒቱ ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸውን ለመወያየት እና ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት በቦታው ተገኝተው ሃይማኖታዊ ግዴታዎትን እንዲወጡ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም እንጠይቃለን። 
በዚህ ጉባኤ ላይ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ መምህራን፣ ዘማሪያን እንዲሁም ምሁራን ይገኙበታል።
አስታውሱ August 12, 2012 From 4:00 pm. ጀምሮ በዋሽንግተን ዲሲ
ለተጨማሪ መረጃ:
571-244-2869 ወይም 571-299-0975 ይደውሉ።

Read Full Post »

በዋልድባ ገዳም ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው፥ እስራቱ፣ እንግልቱ፣ ማሳደዱ፣ ድብደባው በፌደራል ወታደሮች እንደቀጠለ ነው ገዳማውያኑ አባቶቻችንም ጩኽታቸውን አቤቱታቸውን በመላው ዓለም ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን እያስተላለፉ ነው፥ ዝምታውም ቀጥሏል መንግሥትም መፍረሱን እንደቀጠለ ነው። ዝምታችን ይብቃ ገዳማውያኑን እና ታሪካዊ ገዳማችንን እንታደግ እንተባበር። 

በተለይ በአሁን ሰዓት ቤተክርስቲያን ልጆቿን የምትፈልግበት ወቅት ላይ ደርሰናል በሃገር ውስጥም ሆነ በውጪ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ስለቅድስት ቤተክርስቲያን ስለሃገራችን ስለገዳማውያኑ በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ ገዳም ውስጥ የሚገኙት ገዳማውያን ለሃገር በጸለዩ፣ ለወገን በለመኑ፣ ለመሪዎች እና ለሃገር ወደ አምላካችን በለመኑ በየገዳሙ ዛሬ እስራት፣ ግርፋት፣ እንግልት እንዲሁም ግድያ እየደረሰባቸው ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ከዚህ የከፋ በቤተክርስቲያናችን ላይ ሊመጣ አይችልም ስለዚህ እግዚአብሔር ያከበራችሁ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ቆሞሳት፣ ካሕናት አባቶች መከኩሳት፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ መምሕራን፣ ዘማሪያን፣ ዲያቆናት እንዲሁም የቤተክርስቲያን ፈርጦች የሆናችኊ ምዕመናን በሙሉ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ከዮዲት ጉዲት እና ከግራኝ መሀመድ በኃላ እንዲህ ዓይነት ፈተና ገጥሟት አያውቅም ስለዚህ ከሊቅ እስከ ደቂት ተባብረን ልዩነታችንን ወደ ጎን ትተን ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ልንታደግ ይገባናል እንላለን።

ዛሬ ቤተክርስቲያን ከእያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ የመክሊቱን እንዲያበረክት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታቀርባለች፣ ገዳማውያኑ የወገን ያለህ እያሉ ነው ስለዚህ በዚህ ታሪካዊ ጥሪ ተቀብለን የበኩላችንን ጥረት ለማድረግ አምላከ ቅዱሳን የጻድቁ አባ ሳሙኤል ዘዋልድ
ባ አምላክ እንዲረዳን ሁላችን ከሕፃን እስከ አዋቂ ወደአምላካችን ልንጸልይ ይገባናል።
ገጸ ምሕረቱን ይመልስልን ለሕዝባችን፣ ለሃገራችን፣ ለቤተክርስቲያናችን አሜን
ለማንኛውም መረጃ በሚከተሉት ሊያገኙን ይችላሉ
savewaldba@gmail.com
Save Waldba Foundation
PO Box 56145
Washington DC 20040

Read Full Post »

·         የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ሠራተኞች በአካባቢው ሕዝብ እየተሳደዱ ነው::
·         ነዋሪው ሠራተኞቹን እስከ ማይ ገባከተማ ድረስ እንዳሳደዳቸው ተነግሯል::
·         የዓዲ አርቃይና ማይ ፀብሪ ወረዳዎች ሓላፊዎች በታሰሩት መነኰሳት እየተወዛገቡ ነው::
·         ከዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም የተወሰዱት አምስት መነኰሳት በዓዲ አርቃይ ፖሊስ ጣቢያ እንደታሰሩ ናቸው::
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 27/2004 ዓ.ም፤ ጁላይ 4/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ ሰኔ 23 ቀን 2004 ዓ.ም÷ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ ከዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም የተወሰዱት አምስት መነኰሳት በዓዲ አርቃይ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ በአንድ ቆርቆሮ ቤት ውስጥ እንደታሰሩ መኾናቸውን የስፍራው ምንጮች ለደጀ ሰላም ገለጹ፡፡

በተጠቀሰው ቀን በአራት ያህል ቶዮታ መኪናዎች በዓዲ አርቃይ ወረዳ ጸጥታ ሓላፊዎች እና በፌዴራል ፖሊስ ኀይሎች ከገዳሙ ከተወሰዱት አምስት መነኰሳት መካከል ሁለቱ ማለትም አባ ተክለ ሃይማኖት እና አባ ኀይለ ሥላሴ ወደ ዓዲ አርቃይ፤ የተቀሩት ሦስቱ ማለትም አባ ገብረ ማርያም (አባ ግርማይ)፣ አባ ኀይለ ኢየሱስ እና አባ ገብረ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ወደ ማይ ፀብሪ (በአንዳንድ ምንጮች ጥቆማ ወደ ዛሬማ ቀበሌ) በኋላም ወደ ዓዲ አርቃይ መመለሳቸው ታውቋል፡፡ በአሁኑ ወቅት አምስቱም መነኰሳት በዓዲ አርቃይ ፖሊስ ጣቢያ በሚገኝ አንድ ቆርቆሮ ቤት ውስጥ ሌላ ሰው ሊጠይቃቸው በማይችልበት ኹኔታ ተቆልፎባቸው እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡

አምስቱ መነኰሳት ለእስር በተዳረጉበት ኹኔታ ላይ የማይ ፀብሪ ወረዳ አስተዳደር ከዓዲ አርቃይ ወረዳ አስተዳደር ጋራ ውዝግብ ውስጥ መግባታቸው ተሰምቷል፡፡ የውዝግቡ መንሥኤ አምስቱ መነኰሳት የተወሰዱበት የዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም በአማራ ብ/ክ/መ ሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኝ በመኾኑና በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ክልል ወደሚገኘው ማይ ፀብሪ ተወስደው በመታሰራቸው ላይ ሓላፊነት ላለመውሰድ ነው ተብሏል፡፡ የዓዲ አርቃይ ወረዳ አስተዳደር በበኩሉ ለአምስቱ መነኰሳት መታሰር የቅርብ ምክንያት የኾነውየስኳር ልማት ፕሮጀክቱ ዶዘር መቃጠልና በሠራተኞቹ ላይ የደረሰው ጉዳት የሚመለከተው በሰሜን ምዕራብ ትግራይ የሚገኘው የማይ ፀብሪ አስተዳደርን እንደሚል ተመልክቷል፡፡

በዚያው በዓዲ አርቃይ ወረዳ የፍትሕና ጸጥታ ዘርፍ ሓላፊው ‹‹ሓላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም›› በሚል ወደ ሲቪል ሰርቪስ እንዲዘዋወሩ መደረጉ ከዚሁ ውዝግብ ጋራ ሳይያያዝ እንደማይቀር ምንጮቹ ያላቸውን አስተያየት ጨምረው ገልጸዋል፡፡
‹‹ሕዝብን ለተቃውሞ ቀስቅሰዋል፤ ከውጭ ሚዲያዎች ጋራ ይገናኛሉ›› በሚል እየተዋከቡ ከሚገኙት ወንድና ሴት የገዳሙ ማኅበረ መነኰሳት መካከል÷ ቅዳሜ ዕለት የተወሰዱት አምስት መነኰሳት÷ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ የዛሬማ ወንዝ ግድብ በሚሠራበት የፕሮጀክቱ ስፍራ ላይ ለተቃጠለው ዶዘርና ለተጎዱት የፕሮጀክቱ ሠራተኞች ‹‹ሓላፊነቱን ውሰዱ›› የሚል ጫና በጸጥታ ኀይሎች እየተደረገባቸው መኾኑን ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡ አምስቱ መነኰሳት ሰኔ ሰባት ቀን 2004 ዓ.ም በዛሬማ ቀበሌ ከክልል፣ ዞንና ቀበሌ አመራሮች ጋራ ስለ ስኳር ልማት ፕሮጀክቱ (ግድቡ ግንባታ) ተደርጎ በነበረው ስብሰባ ተገኝተው የነበረ ሲኾን÷ ከእነርሱም መካከል በስብሰባው ላይ ንቁ ተሳትፎና ግልጽ ተቃውሞ ሲያሰሙ በነበሩቱ ላይ ጫናው በርትቶ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

የዜናው ምንጮች ጨምረው እንዳመለከቱት÷ ፕሮጀክቱ በዋልድባ ገዳም ህልውናና ክብር ላይ ከሚያደርሰው ተጨባጭና ታሳቢ ስጋቶች የተነሣ በአካባቢው የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በያዝነው ሳምንትም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ባለፉት ቀናት ነዋሪው በጦር መሣርያ ሳይቀር የፕሮጀክቱን ሠራተኞች የፕሮጀክቱ ጽ/ቤት እስከሚገኝበት ማይ ገባ ወረዳ (ከተማ) ድረስ እያስፈራራ ማሳደድ መጀመሩም በአስረጅነት ተጠቅሷል፡፡ ከፕሮጀክቱ ስፍራ በእግር አንድ ሰዓት ወደሚወስደው የሠራተኞች መኖርያ እና የፕሮጀክቱ ጽ/ቤት ወደሚገኝበት ማይ ገባ ከተማ እግሬ አውጭኝ ብለው ከሸሹት ሠራተኞች መካከልም በጥይት ተመትተው የቆሰሉ ሳይኖሩ እንደማይቀር ተገምቷል፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን።

Read Full Post »

በዋልድባ ሰቋር ኪዳነምሕረት የሴቶች አንድነት ገዳም አባቶች እና እናቶች በሱባኤ ባሉበት ወቅት የመንግሥት ታጣቂ ወታደሮች ወደ ገዳሙ ክልል በመግባት 5 አረጋውያን መነኩሳትን ለእስር ዳርገዋቸዋል ምክንያታቸውም ሕዝቡን የምታነሳሱት እናንተ ናችሁ ለዓመጽ እና ለጦርነት አነሳሳችሁት በሚል ሰበብ ነው። እውነታው ግን እያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ ለሃይማኖቱ እና ለቤተክርስቲያኑ ክብር መቆም ያለበት መሆኑን ሁላችንም ጠንቅቀን እናውቃለን። እነዚህ አባቶች ለሀገር፣ ለወገን፣ ለመሪዎችን እንዲሁም ለአለም በጸለዩ የአባቶቻችንን ርስት አንሰጥም ባሉ እስር መዳረጋቸው ትልቅ ቁጣ አስተስቷል በዓለም ዙሪያ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን እባካችሁ ዝም አንበል የአባቶቻችን ደም ይጠራናል የበኩላችንን እናድርግ ስለ እመብርሃን የጭንቅ አማላጇ ብላችሁ ቤተክርስቲያንን እንጠብቅ
“እስከ ሞት ድረስ የታመንክ ሁን” ራዕይ 10:3

ቸር ወሬ ያሰማን

Read Full Post »

Older Posts »

አኰቴት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ Akotet Ze-Orthodox Tewahedo

የዋልድባ ገዳም ታሪካዊ፣ ጥንታዊ፣ ቅዱስ የጸሎት እና ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ቦታ ነው። ቅድስናውንም ከሰው የተሰጠው ሳይሆን በመድኅኒታችን በመድኅኒዓለም ክርስቶስ የተሰጠው ስለሆነ ቦታው ቅዱስ ነው፥ ቅድስናውን ጠብቀን ለትውልድ ማውረስ የእኛ ዋነኛ ዓላማችን ነው።

የዋልድባ ገዳም ታሪካዊ፣ ጥንታዊ፣ ቅዱስ የጸሎት እና ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ቦታ ነው። ቅድስናውንም ከሰው የተሰጠው ሳይሆን በመድኅኒታችን በመድኅኒዓለም ክርስቶስ የተሰጠው ስለሆነ ቦታው ቅዱስ ነው፥ ቅድስናውን ጠብቀን ለትውልድ ማውረስ የእኛ ዋነኛ ዓላማችን ነው።

አደባባይ

የዋልድባ ገዳም ታሪካዊ፣ ጥንታዊ፣ ቅዱስ የጸሎት እና ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ቦታ ነው። ቅድስናውንም ከሰው የተሰጠው ሳይሆን በመድኅኒታችን በመድኅኒዓለም ክርስቶስ የተሰጠው ስለሆነ ቦታው ቅዱስ ነው፥ ቅድስናውን ጠብቀን ለትውልድ ማውረስ የእኛ ዋነኛ ዓላማችን ነው።

አሐቲ ተዋሕዶ AHATI TEWAHEDO

የዋልድባ ገዳም ታሪካዊ፣ ጥንታዊ፣ ቅዱስ የጸሎት እና ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ቦታ ነው። ቅድስናውንም ከሰው የተሰጠው ሳይሆን በመድኅኒታችን በመድኅኒዓለም ክርስቶስ የተሰጠው ስለሆነ ቦታው ቅዱስ ነው፥ ቅድስናውን ጠብቀን ለትውልድ ማውረስ የእኛ ዋነኛ ዓላማችን ነው።

ስንክሳር (Senksar)

የዋልድባ ገዳም ታሪካዊ፣ ጥንታዊ፣ ቅዱስ የጸሎት እና ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ቦታ ነው። ቅድስናውንም ከሰው የተሰጠው ሳይሆን በመድኅኒታችን በመድኅኒዓለም ክርስቶስ የተሰጠው ስለሆነ ቦታው ቅዱስ ነው፥ ቅድስናውን ጠብቀን ለትውልድ ማውረስ የእኛ ዋነኛ ዓላማችን ነው።

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/በሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ – ማኅበረ ቅዱሳን

የዋልድባ ገዳም ታሪካዊ፣ ጥንታዊ፣ ቅዱስ የጸሎት እና ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ቦታ ነው። ቅድስናውንም ከሰው የተሰጠው ሳይሆን በመድኅኒታችን በመድኅኒዓለም ክርስቶስ የተሰጠው ስለሆነ ቦታው ቅዱስ ነው፥ ቅድስናውን ጠብቀን ለትውልድ ማውረስ የእኛ ዋነኛ ዓላማችን ነው።

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ማኅበረ በዓለ ወልድ ሰሜን አሜሪካ

የዋልድባ ገዳም ታሪካዊ፣ ጥንታዊ፣ ቅዱስ የጸሎት እና ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ቦታ ነው። ቅድስናውንም ከሰው የተሰጠው ሳይሆን በመድኅኒታችን በመድኅኒዓለም ክርስቶስ የተሰጠው ስለሆነ ቦታው ቅዱስ ነው፥ ቅድስናውን ጠብቀን ለትውልድ ማውረስ የእኛ ዋነኛ ዓላማችን ነው።

አንድ አድርገን

የዋልድባ ገዳም ታሪካዊ፣ ጥንታዊ፣ ቅዱስ የጸሎት እና ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ቦታ ነው። ቅድስናውንም ከሰው የተሰጠው ሳይሆን በመድኅኒታችን በመድኅኒዓለም ክርስቶስ የተሰጠው ስለሆነ ቦታው ቅዱስ ነው፥ ቅድስናውን ጠብቀን ለትውልድ ማውረስ የእኛ ዋነኛ ዓላማችን ነው።

የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views

የዋልድባ ገዳም ታሪካዊ፣ ጥንታዊ፣ ቅዱስ የጸሎት እና ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ቦታ ነው። ቅድስናውንም ከሰው የተሰጠው ሳይሆን በመድኅኒታችን በመድኅኒዓለም ክርስቶስ የተሰጠው ስለሆነ ቦታው ቅዱስ ነው፥ ቅድስናውን ጠብቀን ለትውልድ ማውረስ የእኛ ዋነኛ ዓላማችን ነው።

dejeselam

4 out of 5 dentists recommend this WordPress.com site

%d bloggers like this: