በመላው ዓለም የተካሄደው ሕዝባዊ ትዕይንት
በመጋቢት ፲፮ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. ቁጥራቸው ከ1200 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በዋሽንግተን ዲሲ ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተገኝተው ተቃውሞዋቸውን አሰምተዋል፣ ነገር ግን የኤምባሲው ኃላፊዎች የተለያየ ምክንያቶችን በመፍጠር ለሰላማዊ ሰልፉ ከወጡት ተወካዮች የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች ተቀብለን ልናነጋግራችሁ ፈቃደኛ አይደለንም ብለው እንደምክንያት ያቀረቡት ኢ.ሐ.ፓ. የተባለው ድርጅት እዚህ ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ስለተገኙ ይህንን ፓርቲ ደግሞ የቀድሞው የደርግ መንግስት ያሸነፈው ፓርቲ ስለሆነ ከእነሱ ጋር ምንም ዓይነት ንግግርም፣ ግንኙነትም የለንም የሚል መልስ ነበር ለሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪዎች የተሰጠው መልስ፥ እንደእውነቱ ከሆነ የሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪዎችም ሆኑ በአጠቃላይ በሰልፉ የተገኘው 99% የሚሆነው በእነዚህ የፓርቲው ሰዎች ሊወክሉት አይችሉም፣ ሰዎቹ በቁጥር እንኳ ሃያ የማይሞሉ እንዴት ይህን የኅብረተሰቡን ክፍል ሊወክሉ ይችላሉ ተብለው ሲጠየቁ፣ በሚቀጥለው ቀን መጥታችሁ ደብዳቤያችሁን ልታቀርቡ ትችላላችሁ ነገር ግን ለዛሬ በራችን ለእናንተ ዝግ ነው በማለት ነበር የመለሱት። የሰልፉ አስተባባሪዎችም ደብዳቤውን በUS Post office በኩል በcertified letter ለኤምባሲው ልከዋል የደብዳቤውን ሙሉ ቃል ለማየት እዚህ ይጫኑ
ቸር ይግጠመን
ዋሽንግተን ዲሲ (Washington, DC) March 26, 2012
ኒውዮርክ ሲቲ (New York City) March 26, 2012
ቤይ ኤሪያ ካሊፎርኒያ (San Jose, CA) April 29, 2012
ዝምታ ይብቃ! ድምጻችንን እናሰማ! |
ለታላቁ ገዳም በቶሮንቶ የተካሄደ ሕዝባዊ ትዕይንት በESAT ዘገባ ላይ
በቶሮንቶ ካናዳ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን “የገዳማቱ ህልውና ይከበር!” በማለት ድምጻቸውን አሰምተዋል፣ ይህ ባለፈው ሳምንት የተደረገው ሰላማዊ ሕዝባዊ ትዕይንት በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ እንዲሁም የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች እንዲሁም ምዕመናን እና ምዕመናት የተገኙበት ትዕይትንት ብዙ ኢትዮጵያውያንን ያሳተፈ ነበር። የኢትዮጵያ ገዳማት ህልውና ይከበር!
በ June 4, 2012 ሊደረግ የታሰበው ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በመላው ዓለም |
Leave a comment