Feeds:
Posts
Comments

Archive for January, 2013

·       “የትግራይ ክልል ተወላጅ ካልሆናችሁ በዚህ ገዳም መኖር አትችሉም” ተብለናል፤

·       “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዋልድባ የሚለውን ስም መጥራት ሁሉ የተለየ ይዘት እየተሰጠው” ነው፤
  •       መነኮሳት ይታሰራሉ፤ ይደበደባሉ፤
  • ከክልሉ ፕሬዚዳንት ጋር ተነጋግረዋል ተብሏል።
(ደጀ ሰላም፤ ጥር 12/2005 ዓ.ም፤ ጃኑዋሪ 20/2013/ PDF)፦ የዋልድባ የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ቤተ-ሚናስ ማኅበረ መነኮሳት አቤቱታቸውን ለአማራ ብሐየራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እና ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አቀረቡ። በመነኮሳት ላይ የሚደርሰውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ የዘረዘረው ደብዳቤው የክልሉ መንግሥት በሰላማውያን መነኮሳት ላይ የሚደርሰውን እንግልት እንዲያስቆም ጠይቀዋል። የታሰሩ፣ የተንገላቱ፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰት የደረሰባቸውን መነኮሳትም ዝርዝር አቅርበዋል። ሙሉ የደብዳቤው ሐሳብ ቀጥሎ ሰፍሯል።

የክልሉ መንግሥት የመናንያኑን አቤቱታ ይቀበል ይሆን? የምናየው ይሆናል።

ቸር ወሬ ያሰማን አሜን

Read Full Post »

አንድ አድርገን (ጥር 05 -2005)፡– መንግሥት በዋልድባ አካባቢ እገነባዋለሁ የሚለውን የስኳር ፕሮጀክት ከጀመረ ወራት ተቆጥረዋል ፡፡ አንድ ጊዜ በጸባይ ሌላ ጊዜ ደግሞ በፈርኦናዊው ጡንቻው በማስፈራራት አላማውን ከግብ ለማድረስ ብዙ እየሞከረ ይገኛል ፡፡ መነኮሳቱን በጎጥና በቋንቋ እንዲከፋፈሉ ሁለትም ሃሳብ እንዲሆኑ ብዙ ጥሯል ፤ ዋልድባ ገዳም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታላቅ ገዳም መሆኑን ወደ ኋላ በማለት ቦታውን የትግራይ ክልላዊ መንግስት አካል እንጂ የአማራ ክልላዊ መንግስት አይደለም ስለዚህ በገዳሙ ላይ ሃሳብ መስጠት የሚችሉት የክልሉ ተወላጅ የሆኑት መነኮሳት እንጂ ማንም አይደለም የሚል ሃሳብ በማንሳት ጉዳዩን ወደ ሌላ መንገድ ለመውሰድ ተሞክሯል ፤  በየጊዜው በቦታው ላይ የሚካሄደው ነገር ለመገናኛ ብዙሃን በማሳወቅ ሃይማኖታዊ ግዴታቸውን በመወጣት ላይ የሚገኙትን አባት እሳቸውን ለጠቆመ የኮንዶሚኒየም ቤት እና ብዙ ሺህ ብር እንደሚሰጠው መንግሥት ለአካባቢው ነዋሪዎች ሲገልጽ ተስተውሏል ፤ ግንባታውን የጀመሩት አንድ ሀገር በቀል እና አንድ አለም አቀፍ ተቋማት ስራውን በተለያዩ ምክንያቶች መስራት ተስኗቸው በአሁኑ ወቅት ሶስተኛ አለም አቀፍ ኮንትራክተር ወደ ቦታው ለሁለቱ ያልተሳካውን ሊሞክር ስራውን ጀምሯል ፡፡ የሥኳር ኮርፖሬሽን ኃላፊ አቶ አባይ ጸሃዬ ለኢቲቪ እንደተናገሩት ከሆነ ሶስተኛው ኮንትራክተር ስራውን ከመጀመሩ በፊት በዛሬማ አካባቢ የሚሰራው ግድብ ጥቂት በሚያሰራ መልኩ ማስተካከያ እንደታከለበት ጠቁመዋል፡፡ የቦታውን ሁኔታ ለቪኦኤ የገለጹት መነኩሴ እንዳሉት አዲስ የገባው ኮንትራክተር የጣሊያል ዜግነት ያላቸው ሲሆኑ “መነኮሳቱ ከአካባቢው ካለቀቁ ስራውን ለመስራት እንቸገራለን” እንዳሉ ገልጸዋል፡፡

(more…)

Read Full Post »