Feeds:
Posts
Comments

Archive for the ‘Uncategorized’ Category

በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

በትላንትናው ዕለት መስከረም ፳፯ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ክርስቲያኖች አንድነት (ዋልድባን ለመታደግ የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ ኮሚቴ ዋሽንግተን ዲሲ ንዑስ ክፍል) አስተባባሪነት የተጠራው ጉባኤ ተካሂዶ ውሏል። በጉባኤውም ላይ ካህናት አባቶች፣ ሰባኬ ወንጌል፣ እንዲሁም በርካታ ከዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው በመጡ የጉባኤው ታዳሚዎች በተገኙበት በርካታ ቁም ነገሮችን ተነጋግሮ እና ጉባኤው ተጠቃሏል። በቀጣይነትም ሥራዎችን በእቅድ ይዞ ለመሥራት ብሎም በአባባቢው የሚገኙትንም መዕመናን እንዲሁም በመላው ዓለም የሚገኙትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኞችን በማስተባበር ለሥራ የተነሳሱ ካህናትን፣ መምህራንን፣ ዘማሪያንን፣ በትውልድ ኢትዮጵያውያን የሆኑ በምዕራቡ አለም በተለያየ ሀላፊነት ላይ ያሉትን ምሁራንን እንዲሁም አጠቃላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናን በማስተባበር የዋልድባ ገዳም መፍረስ ሳይሆን አፈሯ እንኳን እንዳትነካ (ሳትነካ) ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ ቁርጠኝነት ያሳዩበት እና በብዙ ሃዘንም እየደረሰ ያለውን እንግልት በተለያየ መልኩ ለማሳየት ተሞክሯል።

(more…)

Advertisements

Read Full Post »

መስከረም ፳፭ ቀን ፳፻፭ ዓም በአዲስ ድምጽ ራሬዮ ቃለመጠይቅ የተደረገላቸው የዋልድባው ገዳም አባት “እኛ ያልነው ገዳማችሁን ጠብቁ፣ ቅርሳችሁን ጠብቁ ፣ ታሪካችሁን ጠብቁ ነው” ያልነው ለሃይማኖታችን መቆም እንዴት ፖለቲከኛ ያስብለናል ነበር ያሉት። በሀገር ውስጥም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጪ የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያን ታሪካቸውን እና ገዳማቸውን የመጠበቅ ብሎም ለተተኪው ትውልድ የማስተላለፍ ሃላፊነት እንዳለባቸውም አበክረው ገልጸዋል።
ልብ ያለው ልብ ይበል ነበር ያሉት
የአባቶቻችን የጸሎታቸው በረከት ከእኛ ጋር ይሁን

Read Full Post »

የገዳማውያኑ የጸሎታቸው በረከት ይደርብን

·         አቶ አባይ ፀሐዬ የጀመሩትን እጅ የመጠምዘዝ ስራ እንደሚቀጥሉ ይገመታል

·         ባለፈው ከአቶ አባይ ፀሐዬ ጋር የተገናኙት መነኮሳት ተቃውሞ ገጠማቸው

·         ክንፈ ገብርኤል የተባሉት መናኝ ታስረው ወደ ማይ ጸብሪ መወሰዳቸው ተዘገበ

·         ቤተክህነቱ በዝምታው እንደቀጠለ ነው

PDF ለማንበብ ይጫኑ

በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በርካታ የመንግሥት ባለ-ሥልጣናት ወደ ዋልድባ በመሄድ የሦስቱንም ማኅበራት አባቶች እንደሚያነጋግሩ ተነግሯል። የዋልድባ መነኮሳት እና ማኅበራቱ በጠቅላላው ምንም ዓይነት በገዳሙ ስም ድርድር ማድረግ እንደማይፈልጉ እና እንደማይችሉ ቢገልጹም ነገር ግን አቶ አባይ ጸሐዬ፣ አቶ በረከት ስምዖንን ጨምሮ በርካታ የመንግሥት ባለስልጣናት ወደ ቦታው በመሄድ ቢቻልም እጅ ጠምዝዞ ለማሳመን እና የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ በቀጣይነት ስራውን እንዲቀጥል ለማግባባት ወደ ቦታው ለመሄድ በዝግጅት ላይ እንደሆኑ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያሳያል። የገዳሙ አባቶች የሰቋር ኪዳነ ምሕረት የአንድነት ገዳም፣ የዳልሻህ ኪዳነምሕረት ገዳም፣ እንዲሁም የአበረንታት ገዳም ተጠሪዎች በጉዳዩ የተነጋገሩበት ሲሆን እነሱም ውሳኔው የእነሱ ማለትም የገዳማውያኑ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች በሙሉ ውሳኔ እንደሆነ እና በእነሱ በኩል ሊመጣ የሚችለውንም ፈተና በሰማዕትነት እንደሚቀበሉት እና በዚህ ቅዱስ ቦታ ምንም ዓይነት ድርድር ሊገባም እንደማይገባ እና መነኮሳቱ ብቻቸውን ለመወሰን መብት እንደሌላቸውም ተናግረዋል።

(more…)

Read Full Post »

PDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

(ደቂቀ ናቡቴ መስከረም 15/2005) “የጻድቅ ሰውጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።”ያዕ.5:16በዋልደባ ገዳም መንግስት በጀመረው የስኳር ፋብሪካብዙ በጣም ብዙ በደሎች በመነኮሳቱ ደርሷልእየደረሰም ነው፡፡ እስከአሁንም ችግሩ እልባት ሳያገኝበመነኮሳቱ ላይ ደብደባ እንግልት እና ከገዳሙእንዲሰደዱ እየተደረገ ነው ፡፡
መነኮሳቱ ግን መፍትሄው እግዚአብሔር እንደሆነ ሁሉእንባቸው ወደ አምላክ እየረጩ አምላክን ከመማፀንአልቦዘኑም፡፡ እንባን የሚያብስ አምላክ ግን ሁሉንነገር በጊዜው ያደርጋል እያደረገም ነው የሚማር እናከጥፋቱ የሚመለስ የለም እንጂ፡፡ ከዚህ በታችያለውን ጽሑፍ ያደረሱን “ፍቅር ይሄይስ ” የተሰኙፀሐፊ ሲሆኑ እኛም ጽሁፉ የያዘውን ቁመ ነገርለእናነተም ልናካፍላችሁ ወደድን ፀሀፊውን አምላክበእድሜ በፀጋ ይጠብቅልን፡፡ መልካም ንባብ፡፡ አምላካችን ሃገራችንን ይጠብቅልን፡፡  ቸር ወሬ ያሰማን፤አሜን።
  ” ካልጠፋ ገላ ዓይን ጥንቆላ “
  የሰው ልጅ ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ እርስ በርሱ፣ በሀሳብና በድርጊቱ መካከል አለመግባባት ይፈጠራል፡፡ለዚህም የአዳምን ልጆች የአቤልንና የቃዬልን ህይወት ማንሳት የሰው ልጅ በተፈጠረ ማግስት አለመግባባትናየጥቅም እንደራሴነት አንደተጀመረ በቂ ማስረጃ ነው፡፡ በዘመናችን ከጉንጭ አልፋ ክርክርና ንትርክ አስከከፋ ግጭትና ሞት የሚያበቁ አለመግባባቶች የሚከሰቱት አንድም በስልጣን ወይም በጥቅም ይገባኛል የተነሳነው፡፡በነዚህ የግጭት ሰበቦች የተነሳ አለማችን ብዙ ሚለዮን ሰወችንና ብዙ ሀብትን አላግባብ አጣለች፡፡ምናልባት የሰው ልጅ የአስተሳስብ አድማሱ እየጨመረ በመጣ ቁጥር ግን ልዩነቶችን ሰላማዊ በሆነ መንገድየመፍታት ሂደቱ እየጨመረ መምጣቱ ለመጭዋ ዓለም አበረታች ተስፋ ነው፡፡ የሰው ልጅ ከሶስት ነገሮች ጋርሊጣላ ይችላል፡፡
1.    ከሰው ልጅ ጋር
2.   ከተፈጥሮ (ከእንስሳት፣ከእፅዋትና ከአየር ንብረት) ጋር እና
3.   ከፈጣሪ ጋር

Read Full Post »

የገዳማውያኑ የጸሎታቸው በረከት ይደርብን
  • ቅዱስ ራጉኤል በእለተ ቀኑ በዋልድባ ዛሬማ ወንዝ ላይ የተሰራውን ድልድይ በመብረቅ ተመቶ ጠራርጎ ወስዶታል
  • በአቲካ ወንዝ ላይ የተሰራው የሸንኮራ ማልማያ ግድብ እንዲሁ በዚሁ ቀን ፈራርሷል
  • የገዳማውያኑ እንግልት እንደቀጠለ ነው
  • ቤተክሕነት በዋልድባ ገዳም ለሚፈርሱት ቤተክርስቲያኖች ካሳ ጠይቋል ይባላል (የተረጋገጠ መልስ ማግኘት አልቻልንም)
(PDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ )
ባለፉት ጥቂት ሳምትታት ውስጥ በዋልድባ ገዳም አካባቢ በሚሰራው የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ የቻይናው ኮንስትራክሽን ካምፓኒ ሥራውን ቀን ከሌሊት በመስራት ላይ እንደነበረ ከአካባቢው በደረሱን መረጃዎች ለመገንዘብ ችለናል። እንደሚታወቀው ከጥቂት ወራት በፊት በዋልድባ ገዳም አካባቢ ሊሰራ የታሰበውን ፕሮጀክት ሙሉ ለሙሉ ሃላፊነቱን ወስዶ ሥራዎቹን ጀምሮ የነበረው የሱር ኮንስትራክሽን በተለያየ ጊዜ በአካባቢው በደረሰው ተአምራት ለምሳሌ ለመጥቀስ ያህል የዲሳይን ኢንጂነሩ በአጋጣሚ በመሞቱ፣ ጥቂት ሰራተኞች በአውሬ በመበላታቸው፣ የግድቡ ሥራ በጣም አዳጋች በሆነ መልኩ መስራት ባለመቻላቸው (ለግድብ ሥራ ጉድጓድ ቆፍረው በነጋታው ሲመለሱ ውሃ ሞልቶት ወይንም አፈር ተንዶ በመሞላቱ) ተደጋጋሚ ክስተቶች በመፈጸማቸው የሱር ኮንስትራክሽን ኮንትራቱን አፍርሶ መውጣቱ ይታወሳል። ኮንትራት አፍርሶ መውጣት (breach of contract) በብዙ ሚሊዮን ብር ቅጣት የሚያስቀጣ ቢሆንም ሱር ኮንስትራክሽን ባለቤቶቹም ኢትዮጵያውያን በመሆናቸው የእግዚአብሔርን ተአምራት በዓይናቸው በማየታቸው ቅጣቱን ተቀጥተው ትተው ወጥተው ነበር።

Read Full Post »

  • ለአገራችን መልካም መሪ ለቤተ ክርስቲያናችንም ደገኛ አባት እንዲሰጥ ጸሎት ይደረጋል::
  • የተቀጸል ጽጌና መስቀል ደመራ በዓላት አከባበር ዝግጅት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማሳሰቢያ ተሰጥቷል::
  • የአገር ሽማግሌዎች ቡድን በዕርቀ ሰላሙ ጉዳይ ከቅ/ሲኖዶስ ጋራ ይወያያል::
  • ነገ ከሚጀመረው የማኅበረ ቅዱሳን ዐሥረኛ ጠቅላላ ጉባኤስ ምን እንጠብቅ?

(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 29/2004 ዓ.ም፤ September 4/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በቀድሞው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ኅልፈተ ሕይወት ታውጆ የሰነበተውና ሀገሪቱን ማቅ ያለበሳት ብሔራዊ የሐዘን ቀን ካበቃና ሐዘኑን በተለያየ መንገድና በተለያየ መንገድ ሲገልጽ ለቆየው የተለያየ የኅብረተሰብ ክፍል  ወደ መደበኛ የሥራ እንቅስቃሴው እንዲመለስ ከተጠየቀ፣ ዝቅ ብሎ ሲውለበለብ የቆየው ሰንደቅ ዓላማ ወደ መደበኛ ከፍታው ከተመለሰ በኋላ ለሁለት ሱባኤ ያህል (ዐሥራ ሦስት ቀናት) የቆየው ብሔራዊ ሐዘን ማብቃቱ ከወደ ቤተ መንግሥት በተገለጸበት ዕለት የሁለት ሱባኤ ጸሎተ ምሕላ ደግሞ ከቤተ ክህነት በኩል ታውጇል፡፡ ለሁለት ሱባኤ ማለትም ለዐሥራ አራት ቀናት የሚዘልቀው የጸሎተ ምሕላ ሱባኤ ጳጉሜን 1 ቀን 2004 ዓ.ም በዘመነ ዮሐንስ ተጀምሮ መስከረም 10 ቀን 2005 ዓ.ም በዘመነ ማቴዎስ የሚፈጸም ነው፡፡ የጸሎተ ምሕላው ሱባኤ የታወጀው በትናትናው ዕለት ተጀምሮ ዛሬም ቀጥሎ በዋለው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ነው፡፡
(more…)

Read Full Post »

በዋልድባ አብረንታንት ገዳም መነኰሳት ላይ ባተኰረውና ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ እየተባባሰ በቀጠለው እስርና እንግልት ሳቢያ ከስድስት ያላነሱ መነኰሳት የፀለምት – ማይ ፀብሪ የፀጥታ ኀይሎች በሚያደርሱባቸው ግፍ ሳቢያ ወደ ሌሎች ገዳማት መሰደዳቸውን፣ በተቀሩትም አባቶች ላይ ድብደባ እየተፈጸመባቸው መኾኑን የሥፍራው ምንጮች እየገለጹ ናቸው፡፡
የዜናው ምንጮች እንደሚያስረዱት÷ የወረዳው ፖሊሶችና ታጣቂዎች በገዳሙ መነኰሳት ላይ የሚፈጽሙት እንግልትና ድብደባ የተባባሰው የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ኅልፈተ ሕይወት መሰማቱን ተከትሎ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽኑ ሕመም እና ኅልፈት ገዳማውያኑን ተጠያቂ በማድረግ ነው፡፡ ቀደም ሲል በየጊዜው እየታሰሩ በተለቀቁት አበው መነኰሳት ላይ ያነጣጠረው ይኸው ርምጃ በአሁኑ ወቅት ደግሞ መነኰሳቱ ጨርሶ ገዳሙን ለቀው እንዲወጡ ከማዘዝና ከማስገደድ ጋራ የተያያዘ መኾኑም ተመልክቷል፡፡

Read Full Post »

Older Posts »

አኰቴት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ Akotet Ze-Orthodox Tewahedo

የዋልድባ ገዳም ታሪካዊ፣ ጥንታዊ፣ ቅዱስ የጸሎት እና ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ቦታ ነው። ቅድስናውንም ከሰው የተሰጠው ሳይሆን በመድኅኒታችን በመድኅኒዓለም ክርስቶስ የተሰጠው ስለሆነ ቦታው ቅዱስ ነው፥ ቅድስናውን ጠብቀን ለትውልድ ማውረስ የእኛ ዋነኛ ዓላማችን ነው።

የዋልድባ ገዳም ታሪካዊ፣ ጥንታዊ፣ ቅዱስ የጸሎት እና ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ቦታ ነው። ቅድስናውንም ከሰው የተሰጠው ሳይሆን በመድኅኒታችን በመድኅኒዓለም ክርስቶስ የተሰጠው ስለሆነ ቦታው ቅዱስ ነው፥ ቅድስናውን ጠብቀን ለትውልድ ማውረስ የእኛ ዋነኛ ዓላማችን ነው።

አደባባይ

የዋልድባ ገዳም ታሪካዊ፣ ጥንታዊ፣ ቅዱስ የጸሎት እና ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ቦታ ነው። ቅድስናውንም ከሰው የተሰጠው ሳይሆን በመድኅኒታችን በመድኅኒዓለም ክርስቶስ የተሰጠው ስለሆነ ቦታው ቅዱስ ነው፥ ቅድስናውን ጠብቀን ለትውልድ ማውረስ የእኛ ዋነኛ ዓላማችን ነው።

አሐቲ ተዋሕዶ AHATI TEWAHEDO

የዋልድባ ገዳም ታሪካዊ፣ ጥንታዊ፣ ቅዱስ የጸሎት እና ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ቦታ ነው። ቅድስናውንም ከሰው የተሰጠው ሳይሆን በመድኅኒታችን በመድኅኒዓለም ክርስቶስ የተሰጠው ስለሆነ ቦታው ቅዱስ ነው፥ ቅድስናውን ጠብቀን ለትውልድ ማውረስ የእኛ ዋነኛ ዓላማችን ነው።

ስንክሳር (Senksar)

የዋልድባ ገዳም ታሪካዊ፣ ጥንታዊ፣ ቅዱስ የጸሎት እና ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ቦታ ነው። ቅድስናውንም ከሰው የተሰጠው ሳይሆን በመድኅኒታችን በመድኅኒዓለም ክርስቶስ የተሰጠው ስለሆነ ቦታው ቅዱስ ነው፥ ቅድስናውን ጠብቀን ለትውልድ ማውረስ የእኛ ዋነኛ ዓላማችን ነው።

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/በሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ – ማኅበረ ቅዱሳን

የዋልድባ ገዳም ታሪካዊ፣ ጥንታዊ፣ ቅዱስ የጸሎት እና ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ቦታ ነው። ቅድስናውንም ከሰው የተሰጠው ሳይሆን በመድኅኒታችን በመድኅኒዓለም ክርስቶስ የተሰጠው ስለሆነ ቦታው ቅዱስ ነው፥ ቅድስናውን ጠብቀን ለትውልድ ማውረስ የእኛ ዋነኛ ዓላማችን ነው።

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ማኅበረ በዓለ ወልድ ሰሜን አሜሪካ

የዋልድባ ገዳም ታሪካዊ፣ ጥንታዊ፣ ቅዱስ የጸሎት እና ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ቦታ ነው። ቅድስናውንም ከሰው የተሰጠው ሳይሆን በመድኅኒታችን በመድኅኒዓለም ክርስቶስ የተሰጠው ስለሆነ ቦታው ቅዱስ ነው፥ ቅድስናውን ጠብቀን ለትውልድ ማውረስ የእኛ ዋነኛ ዓላማችን ነው።

አንድ አድርገን

የዋልድባ ገዳም ታሪካዊ፣ ጥንታዊ፣ ቅዱስ የጸሎት እና ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ቦታ ነው። ቅድስናውንም ከሰው የተሰጠው ሳይሆን በመድኅኒታችን በመድኅኒዓለም ክርስቶስ የተሰጠው ስለሆነ ቦታው ቅዱስ ነው፥ ቅድስናውን ጠብቀን ለትውልድ ማውረስ የእኛ ዋነኛ ዓላማችን ነው።

የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views

የዋልድባ ገዳም ታሪካዊ፣ ጥንታዊ፣ ቅዱስ የጸሎት እና ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ቦታ ነው። ቅድስናውንም ከሰው የተሰጠው ሳይሆን በመድኅኒታችን በመድኅኒዓለም ክርስቶስ የተሰጠው ስለሆነ ቦታው ቅዱስ ነው፥ ቅድስናውን ጠብቀን ለትውልድ ማውረስ የእኛ ዋነኛ ዓላማችን ነው።

dejeselam

4 out of 5 dentists recommend this WordPress.com site

%d bloggers like this: