- የአዲርቃይ ፍርድ ቤት ገዳማችን አይታረስም በማለታቸው ወጣቶችን በአሸባሪነት ከሰሰ
- በዛሬማ የሚገኙ ነዋሪዎች በወጣቶቹ ላይ ምስክርነት አንሰጥም በማለታቸው እንግልት እየደረሰባቸው ነው
- የሰሜን ጎንደር ጸጥታ ክፍል ክሱ በአሸባሪነት መሆን አለበት በማለት ትዕዛዝ አስተላልፏል
- የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከገዳሙ በረከት ለመቀበል የመጡት ማስፈራሪያ እና ፍተሻ (strip search) ተደረገባቸው
- የጣሊያኑ ኮንስትራክሽን ሌላ አማራጮችን እንፈልግ ብሏል
- የወልቃይት ነዋሪም እርሻውን እንዲቀጥል እስከሚመጣው ዓመት ምንም ነገር እንደማይኖር እየተነገረው ነው
ሙሉውን በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የዛሬ ዓመት አካባቢ ይሆናል የዛሬማ ወጣቶች ከመንግሥት ጋር ገዳማችን አይታረስም፣ የአባቶቻችንን ድንበር አናስነካም በማለት ከመንግሥት ታጣቂዎች ጋር ግብግብ የተፈጠረው፥ በወቅቱ የክልሉ ባለሥልጣናት በቦታው ተገኝተው ከዛሬማ ነዋሪዎች ጋር ስብሰባ አድርገው የዛሬማን ነዋሪ ውሳኔ እንዲሰጥ እያስፈራሩ ባሉበት ወቅት ነበር ጥቂት ወጣቶች የአባቶቻችንን ድንበር አናስነካም፣ ገዳማችንንም ፈቅደን አናሳርስም በማለታቸው ጥቂቶቹን በወቅቱ ወደ እስር ቤት ሲከቷቸው የተቀሩት አምልጠው ጫካ ገብተው ገዳማችንን ማንም ሊነካውም፣ ሊደፍረው፣ ሊረግጠውም አይገባም በማለት ጥሪያቸውን ሲያቀርቡ ቆይተዋል የአካባቢውንም ገበሬ ማኅበራት፣ የሃገር ሽማግሌዎችን በማነጋገር እንዴት ዓይናችን እያየ ገዳማችንን የማንም አማቄላውያን (አረማውያን) መፈንጫ ይሆናል፣ ይሄ ቦታ እኮ የቅዱሳን ማረፊያ፣ የግዑሳን መጠጊያ ለእኛ ለተዳደፍነው እረፍት፣ በረከት፣ ቅድስና ለማግኘት የምንሄድበት እንጂ እንዴት እነዜህ አረማውያን ዛሬ እንደፈለጉት ያደርጉታል በማለት ተቃውሟቸውን በከተማው አስተዳደር ጽ/ቤት ከሃገረ ስብከቱ ሃላፊዎች ቢያቀርቡም የተወሰኑ የመንግሥት ሃላፊዎች በሃገር ሽማግሌዎች ምከሯቸው እና ወደ ቤታቸው እና ቤተሰባቸው ይመለሱ በማለት አግባብተው ወደ ሃገራቸው እና ቤተሰባቸው ከተቀላቀሉ የሦስት ወይም ሁለት ወር አይበልጣቸውም ነበር።
የኢትዮጵያ መንግሥት ሊያስገነባቸው ያሰባቸው የስኳር ፋብሪካዎች
ወጣቶቹም ወደ ሃገራቸው እና ወደ ቤተሰቦቻቸው እንደተመለሱ ብዙም ሳይቆይ የአዲርቃይ ከተማ አቃቤ ሕግ ቢሮ ደብዳቤ ከሰሜን ጎንደር የጸጥታው ቢሮ ይደርሰዋል በደብዳቤውም ላይ “ከዚህ በፊት ታስረስው እና በምሕረት የተመለሱት ወጣቶች በሙሉ በአሸባሪነት፣ በመንግሥት ላይ በመነሳት፣ እና ከግንቦት 7 ታጣቂዎች ጋር በመተባበር” በአስቸኳይ እንዲከሰሱ እና የፍርዱንም ሄደት እንደሚከታተሉት ጠቅሰው ደብዳቤ ይጽፋሉ። ደብዳቤ የደረሳቸው የአቃቢ ሕጉ ቤሮ ሰራተኞች ወደ ዛሬማ በመሄደ ከከተማው የመንግሥት ተወካዮች እና የጸጥታው ሃላፊዎች ጋር መመካከር ይጀምራሉ፥ የዛሬማ ከተማ መስተዳደር እና የጸጥታው ሃላፊዎች እንዴት ብለን ነው በአሸባሪነት የምንከሳቸው? በምን መረጃ ነው ብለው ሲጠይቁ ሰዎችን አስመስክሩባቸው በማለት የአቃቢ ሕጉ ሰራተኞች ቢጠይቁም ጥቂት የአካባቢው ነዋሪዎች ተጠርተው የምስክርነት ቃላቸውን እነሱ በሚፈልጉት መልኩ ከመሰከቱ ወሮታውን መንግሥት እንደሚሰጣቸው ቢያብሏቸውም “እኛ በልጆቻችን ላይ የሃሰት ምስክር ልንሆን አንችልም፣ የምናውቀው ነገር ቢኖር ገዳማችንን አትንኩ ማለታቸውን ነው በማለት እንቢታቸውን ገልጸዋል” የአካባቢው ነዋሪዎችም እንሰዛሬ ድረስ ሰዎችን እንዲህ እየደረጉ ነው ለካ በሃሰት እየከሰሱ ያሉት እነኝህ ወጣቶች ያደረጉት ነገር ቢኖር ገዳማችን አትንኩ ከማለት በስተቀር እንኳን አሸባሪ ሊሆኑ ጭራሽ እንዴት እንዲህ ዓይነት ክስ ሊመሰርትባቸው ይችላል በማለት ቅሬታቸውን ደጋግመው በማሰማት የአካባቢው የጸጥታ ቢሮ እና የአዲርቃይ የአቃቢ ሕግ ሰራተኞች ተመካክረው ወጣቶቹን በአሸባሪነት ቀርቶ በሌላ ክስ ሊመሰርቱባቸው ተስማምተው ነበር ጉዳዩ
Continue Reading »
Like this:
Like Loading...